ትራኮማ አይንን የሚያጠቃ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ሲሆን፤ ክላሚድያ በሚባል ባክቴሪያ መንሰኤነት ይፈጠራል፡፡ በአዳጊ ሃገራት የእይታ መጥፋትን ከሚያስከስቱ ህመሞች ዋነኛው ነው። 85% የትራኮማ ታማሚዎች አፍሪካ ውስጥ ይገኛሉ። እንዲሁም መከላከል ከምንችላቸው እይታን የሚያሳጡ ነገሮችም አንዱ ነው። አይን፣ የአይን ቆብ፣ የአፍንጫ እና ጉሮሮ ፍሳሾች ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
- የአይን ማሳከክ እና የዓይን እና የዐይን ሽፋኖች መቆጣት
- መግል ከዓይን መፍሰስ
- የዐይን ቆብ እብጠት
- ብርሃንን መፍራት(የመጭበርበር ስሜት መፍጠር)
- የዓይን ሕመም
- የዓይን መቅላት
የዓለም ጤና ድርጅት በየደረጃው ትራኮማን ከፍሎታል እነዚህ
- ጥቂት አነስ አነስ ያሉ እብጠቶች የአይን ቆብ ላይ ሲወጡ
- ከፍተኛ የአይን መቆጣት እና ቆብ እብጠት ሲኖር እና አይን ሲቀላ እንዲሁም ብዙ አነስ አነስ ያሉ እብጠቶች አይን ቆብ ላይ ሲወጡ
- በተደጋጋሚ በህመሙ በመጠቃት የተነሳ የአይን ቆብ ላይ ጠባሳ ይፈጠራል ይህም ቆብ ወደ ውስጥ ኢንዲገለበጥ ያደርጋል።
- ቆብ ወደ ውስጥ ሲገለበጥ ያንን ተከትሎ ሽፋሽፍት የአይን የውስጠኛውን ክፍል በመፈግፈግ ያስቆጣዋል።
- ኮርኒያ(ውሃማ ቀለም ያለው የአይን ክርታስ) ላይ ጠባሳ ሲኖር እና እይታን ሲከለክል
- በጣም የተፋፈገ በሆነ ሁኔታ ብዙ ሰዎች አንድ ላይ ሲኖሩ (ቅርብ ንክኪ የመኖሩ እድል ከፍ ስለሚል የመተላለፍ አጋጣሚው ከፍ ያለ ነው)
- ንጽህና የጎደለው አኗኗር(ፊትን ያለመታጠብ)
- ከ4-6 ዓመት እድሜ ላይ ያሉ ህጻናትን የበለጠ ያጠቃል
- ሴቶች 2-4 እጥፍ ከወንዶች የበለጠ ያመያዝ እድል አላቸው (ከህጻናት ጋር የበለጠ ንክኪ ስላላቸው ነው)
- ዝንብ የበዛበት አካባቢ መኖር
- የአይን ቆብ ጠባሳ እና ቆብ ወደ ውስጥ መገልበጥ
- የእይታ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መጥፋት
- የእይታን ማጣት ተከትሎ የሚከሰቱ የግላዊ፣ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች።
- ንጽህናን መጠበቅ እና ፊትን በትክክል በየቀኑ መታጠብ
- ዝንቦችን ከሚኖሩበት አካባቢ ማጥፋት
- ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ
በአብዛኛው በበሽተኛው ምልክት እና የሃኪም ምርመራ ላይ ተመስርቶ የሚታወቅ ስለሆነ የተለየ ምርመራ አይደረግም። አይንን እና ቆብን በደንብ መመልከት ያስፈልጋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ትራኮማን ማከሚያ ብሎ ያወጣቸው SAFE የሚባሉ የህክምና መንገዶች አሉ። የህክምና አማራጮቹ በሃኪሞ የሚወሰኑ ናቸው።
- የቀዶ ህክምና ካስፈለገው በሃኪም ይወሰናል (ጠባሳ ሲፈጠር በተለይ)
- የአይን ጠብታ ወይም የሚዋጥ አንቲባዮቲክ
- መከላከያ መንገዶችን መጠቀም
- ንጽህናን መጠበቅ
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።