ዳማከሴDamakese

የደም መርጋት በሽታ

የደም መርጋት በሽታ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የደም ቧንቧ ውስጥ ደም ሲጓጉል እና ጠጣር መልክ ሲይዝ የሚፈጠር በሽታ ነው። በአልጋ ላይ ተኝተው ለረዝም ጊዜ የሚቆዩ ታማሚዎችን በተለየ የሚያጠቃ ህመም ነው፡፡ ቶሎ ካልታከመ የረጋው ደም ወደ ሳንባ በመሄድ አተነፋፈስ ላይ ችግር በመፍጠር ታካሚውን ለበለጠ ህመም እንዲሁም ሞት ሊያጋልጥ ይችላል። ስለዚህም ምልክቶቹን፣ አጋላጭ ሁኔታዎችን ማወቅ ህመሙን ለመከላከል እንዲሁም ተገቢውን እርዳታ ቶሎ በማግኘት ከአስከፊ ውጤቶች ይጠብቀናል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።