የሃሞት ጠጠር በሃሞት ከረጢት ውስጥ ጠጠር ሲፈጠር የሚከሰት በሽታ ሲሆን በቀዶ ህክምና ዘርፍ በተደጋጋሚ ከሚያጋጥሙ ህመሞች አንዱ ነው። ሃሞት ወደ ትንሹ አንጀት በሃሞት ቱቦ በመጓዝ በጉበት የሚመረት እና በሃሞት ከረጢት የሚጠራቀም ፈሳሽ ሲሆን የምግብ አፈጫጨት ላይ በተለይም ስብ ወደ ሰውነት እንዲመጠጥ በማድረግ ትልቅ አስተዋጾ ያደርጋል። ነገር ግን የሃሞት ዝውውር ላይ ችግር ሲኖር እንዲሁም ውስጡ ያሉት ንጥረ ነገሮች ላይ መዛባት ሲታይ የሃሞት ጠጠር ይፈጠራል።
- የእድሜ ከ40 ዓመት በላይ መሆን
- በጾታ ሴት መሆን
- የስኳር በሽታ
- ቅባት የበዛበት ምግብ ማብዛት
- ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት
- ረዘም ላለ ግዜ ያለመመገብ
- ጨጓራ ላይ የተደረገ ቀዶ ህክምና
አብዛኛውን ጊዜ ህመሙ ምልክት ላያሳይ ይችላል። ነገር ግን ምልክት ሲኖር፡
- በቀኝ በኩል ከጎድን አጥንት ዝቅ ብሎ የሚሰማ ህመም ሲኖር
- ብዙውን ጊዜ ቅባታማ ምግብ ከተመገቡ በኋላ የሚሰማ)
- ይህ ህመም ወደ ጀርባ ሊዞር ይችላል።
- ማቅለሽለ እና ማስታወክ
- ጤናማ የሰውነት ክብደትን መጠበቅ
- ምግብን በአግባቡ መመገብ(ረዥም ጊዜ ያለምግብ መቆየት የለቦትም)
- ቅባት የበዛበትን ምግብ ያለመመገብ
- የሃሞት ከረጢት ኢንፌክሽን ፣ ከአንጀት አንዳንድ ባክቴሪያዎች ወደ ላይ በመውጣት የሃሞት ከረጢትን እንዲያጠቁ የሃሞት ዝውዝውር መደናቀፉ ያመቻቸ ሁኔታን ይፈጥራል። ይህ ሲፈጠር ታማሚዎች፡ ትኩሳት ብርድብርድ ማለት፣ ሃይለኛ እና የማያቋርጥ የሆድ ህመም፣ ማስታወክ እና የመሳሰሉትን ምልክቶች ያሳያሉ።
- ይህ የሃሞት ከረጢት መቆጣት ሲደጋገም ጠባሳ መፍጠር ያመጣል።
- የጉበት ጉዳት፡ የሃሞት ዝውውር ላይ በሚፈተረው ችግር ምክንያት ሃሞት ወደ ጉበት በመመለስ የጉበት መቆጣትን፣ሲደጋገም ደግሞ ጉበት ላይ ጠባሳ በመፍጠር የጉበት ስራን ያስተጓጉላል።
- የሃሞት ጠጠር ከከረጢቱ ወጥቶ ወደ ሃሞት ማለፊያ ቧንቧ ሲገባ ደግሞ፤ የቧንቧው ኢንፌክሽን ያመጣል ምልክቶቹም፡ የሆድ ህመም፣ አይን እና ቆዳ ቢጫ ማሆን፣ ደጋግሞ ማስታወክ፣ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት ናቸው።
- የጣፊያ ጉዳት፡ ጠጠሩ የጣፊያን ፈሳሽን የሚያስተላልፈውን ቧንቧ ከዘጋ የጣፊያ ፈሳሽ በመመለስ እራሱ ጣፊያ ላይ ጉዳትን ይፈጥራል ይህ ሲኖር የሚታዩ ምልክቶች፡ ከፍተኛ የሆድ ህመም(ከእንብርት ከፍ ብሎ ያለው ቦታ የበለጠ የሚሰማ እና ወደ ጀርባ ሚንሰራፋ ፣ ታካሚው ወደ ፊት ዝቅ ሲል ፋታ ያገኛል) ተደጋጋሚ ትውከት፣ መድከም እና ራስ መሳት ይገኙበታል።
- የደም ምርመራ
- የጉበት ሁኔታን ሚያጣራ ምርመራ
- የሆድ አልትራሳውንድ
- የሃሞት ጠጠር ምልክት ከሌለው እና አስከፊ ጉዳቶች ካላደረሰ በክትትል የሚቀጠል ሲሆን እንደ በሽተኛው ሁኔታ በሃኪም የቀዶ ህክምና እንዲደረግ ሊወሰን ይችላል።
- በተጨማሪ ምልክት ሲኖር እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱት ጎንዮሽ ጉዳቶች ሲፈጠሩ ቀዶ ህክምና ማድረግ ብቸኛ አማራጭ ይሆናል።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።