የሚጥል በሽታ በአአምሮ ውስጥ ያለ የኤሌክትሪካል እንቅስቃሴ ከተለመደው በላይ ከፍ ሲል የሚፈጠር ህመም ነው። የሚጥል በሽታ ተብሎ ለመወሰድ ከ2 ጊዜ በላይ እና ከ24 ሰአት ልዩነት በላይ ህጻኑን ሲያጣቃ ነው። የሚጥል በሽታ አይዋቂንም የሚያጥቃ ህመም ቢሆንም እንኳን በህጻናት ላይ የበለጠ ስለሚታይ እሱ ላይ እናተኩራለን።
የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ህመም ሲሆን በምልክቶቹ ላይ በመነሳት ይከፋፈላል እነዚህም፡ -የተወሰነ አካልን ትኩረት አድርጎ የሚያጠቃ የሚጥል በሽታ፡ ይህ የሚከሰተው የአንጎል አንድ ክፋይን የሚያጠቃ የሚጥል በሽታ ሲኖር ነው። ታካሚው ራሱን ሊስት ወይንም ላይስት ይችላል። ምልክቱም፡ የእግር ወይም የእጅ ተለይቶ መንቀጥቀጥ፤የእይታ፣ የመስማት ወይም የማሽተት ስሜቶች መናጋት፣ የስሜት መለዋወጥ ፣የሽንት ወይም ሰገራ ቁጥጥር ማጣት ናቸው። ከላይ እንደተጠቀሰው የተወእሰነ አካልን ለይቶ የሚያጠቃ የሚጥል በሽታ የታካሚው ራስን መሳት ላይ ተመስርቶ ለሁለት ይከፈላል። ይህ የሚጥል በሽታ አይነት አጠቃላይ አካልን ወደሚያጠቃው የሚጥል በሽታ ሊቀየር ይችላል።
- አጠቃላይ አካልን የሚያጠቃ የሚጥል በሽታ፡ አንጎልን ሙሉ በሙሉ የሚያጠቃ ሲሆን የሚፈጠር ሲሆን፣ ምልክቱም፡ ራስን መሳት ፣ የእግርም የእጅም አንድላይ መንቀጥቀጥ፣ የአይን መገለባበጥ፣ የምራቅ ከንፈር ዙሪያ አረፋ መስራት፣ የሰገራ እና የሽንት ቁጥጥር ማጣት።
- የመፍዘዝ ስሜት የሚፈጥር የሚጥል በሽታ፡ ይህ ከአሉት አይነቶች ውስጥ በተለየ በህጻናት ላይ የበለጠ የሚታይ አይነት ሲሆን ምልክቱም፡ ህጻኑ ፈዞ ወደ ሩቅ ይመለከል ብንጠራው አይመልስም፣ የአይን ቆብ መንቀጥቀጥ እና የከንፈር መርገብገብ ያሳያል፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደቀልቡ ይመለሳል።
የተለያዩ መንስኤዎች ያሉት ህመም ነው ከነዚህም ፡በዘር የሚመጣ የሚጥል በሽታ የጭንቅላት መመታት የአንጎል ኢንፌክሽን(የማጅራት ገትር) በወሊድ ጊዜ የጨቅላው መታፈን ከነበረ በእርግዝና ጊዜ የጽንሱ ኢንፌክሽን መኖር በእርግዝና ጊዜ የትንባሆ እና አደንዛሽ እጽ መጠቀም ከነበረ የአንጎል እጢ ጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ይገኙበታል
የሚጥል በሽታ አንዴ ከታወቀ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሊቀሰቀስ ይችላል ለዚህ የሚያጋልቱ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው። -መድሃኒት ማቋረጥ -ከፍተኛ ለሆነ የድምጽ እና የብርሃን መጠን መጋለጥ -መጨናነቅ -የእንቅልፍ እጦት -ትኩሳት እና ኢንፌክሽኖች -የሰውነት ንጥረነገር መዛባት
በሽታው ተነስቶ ሲወድቁ ሰውነት ላይ አደጋ ሊደርስ ይችላል በተደጋጋሚ የሚፈጠር የሚጥል በሽታ የአእምሮ እድገት ላይ አሉታዊ አስተዋጾ ያደርሳል ይህም በትምህርት ላይ ያላቸውን አቅም ይቀንሳል። የስነ-ልቦና ጉዳት ያደርሳል የባህሪ መረበሽ ያመጣል የመርሳት ችግር ያመጣል
-የደምሴል መጠን ማጣሪያ ምርመራ -የስኳር መጠን ማጣሪያ ምርመራ -የሰውነት ንጥረነገሮች መጠን ምርመራ -ኢኢጂ -የጭንቅላት ኤም እር አይ -የኩላሊት እና ጉበት ስራ ማጣሪያ ምርመራ
የሚጥል በሽታ ሲፈጠር እና ከላይ ያሉት ምልክቶች ሲታዩ ቶሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል መምጣት ያስፈልጋል አምቡላንስ እስከሚደርስ ግን ህጻኑን በግራ ጎኑ ማድረግ፤ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ከአካባቢው ማስወገድ መንቀጥቀጡን ለመገደብ አጥብቆ ከመያዝ መቆጠብ ያስፈልጋል። መድሃኒቶቹ - Lamotrigine, Na Valproate, Phenytoin... ናቸው።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።