ዳማከሴDamakese

ኩፍኝ

ኩፍኝ ሚዝልስ በሚባል ቫይረስ የሚከሰት እና በክትባት መከላከል ከሚቻሉ እና ለከፋ ለበሽታ እና ለሞት ከሚዳርጉ ግንባር ቀደም በሽታዎች አንዱ ነው። እንደ ሃገራችን ባሉ አዳጊ ሃገራት በከፍተኛ ድረጃ የሚፈጠር እና ክትባት መሰጠት ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በመጨመሩ እየቀነሰ የመጣ በሽታ ነው። ነገር ግን አሁንም ከፍተኛ የጤና ተቋም ትኩረት ከሚያስፈልጋቸው ህመሞች አንዱ ነው። የሚተላለፈው በመተንፈሻ አካላት (በትንፋሽ፣ በሳል፣ የቀረበ አኗኗር) በኩል ነው። ይህም ቶሎ የመንሰራፋት እድሉን ይጨምራል። ኩፍኝ ሳንባን፣አንጎልን፣ አንጀትን እና ቆዳን በተለየ ሁኔታ ያጠቃል በመሆኑም ቶሎ ተገቢውን ህክምና ያለማግኘት አስከፊ የሆነ ውጤት ያስከትላል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።