ቃር የጨጓራ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ ሲመለስ የሚፈጠር ህመም ነው። ከጨጓራ እና የምግብ ቧንቧ መካከል የሚገኝ እና ምግብ በምንውጥበት ጊዜ ብቻ የሚከፈት ቋት አለ። ይህ ቋት ስራውን በትክክል መስራት ሲያቅተው እና የጨጓራ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ ሲመለስ ከጨጓራ አንጻር አሲዱን የመቋቋም አቅም ስለሌለው የመላጥ ጉዳት ይደርስበታል።
- ደረት ላይ የሚሰማ የማቃጠል ስሜት
- የመምረር ጣእም መፈጠር
- በተደጋጋሚ ማጋሳት
- ደረቅ ሳል
- ከምግብ ቧንቧ መላጥ በተጨማሪ ቃር በተደጋጋሚ ለሚፈጠር የአየር ቧንቧ መቆጣት (ብሮንካይተስ) ያጋልጣል።
- ክብደት መቀነስ
- ምግብ ከበሉ በኋላ ለ3-4 ሰአት ያህል ከመተኛት መቆጠብ
- በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ከመብላት ይልቅ ትንንሽ የምግብ መጠን በተደጋጋሚ መመገብ
- በቂ ውሃ መጠጣት
- ትንባሆ ፣ ጨው እና አቃጣይ ምግቦችን ፣ ቡና፣ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ
- በሚተኙበት ጊዜ ትራስን ከፍ አርጎ መጠቀም።
- ከ6 እስከ 8 ሳምንታት ያህል የጨጓራ መድሃኒት መውሰድ ይኖርቦታል ህመሙን በዚህ መቆጣጠር ካልተቻለ የጨጓራን ቋት ሚያጠነክር
- ቀዶ ህክምና ይደረጋል ይህ በሃኪምች ውሳኔ የሚደረግ የህክምና አማራጭ ነው።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።