ማይግሬን የብዙ ሰዎች የራስ ምታት ህመም መንስኤ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ራስ ቅል ደም የሚያደርሱ ትናንሽ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚኖር ችግር የሚፈጥረው ህመም ነው። ከ4- 72 ሰአታት ያህል የሚቆይ ሲሆን ታካሚዎች የተለመዱ የእለት ከዕለት ተግባሮቻቸውን እንዳያረጉ የሚያግድ ህመም ነው።
- በብዛት ከፍሎ የራስ እና የፊትን ግማሽ የሚያጠቃ ራስ ምታት
- ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ
- ከፍተኛ ድምጽን መቋቋም ያለ መቻል፣
- ብርሃን መጥላት ቀስቃሽ ነገሮች
- ከፍተኛ ድምጽ
- ምግብ ሳይመገቡ መቆየት
- አስጨናቂ ነገሮች ሲያጋጥሙ
- እንቅልፍ እጥረት ህመሙ ሊጀምር ሲል አንደንድ ሰዎች ሚያጋጥሟቸው ምልክቶች አሉ። እነዚህ አውራ ብለን የምንጠራቸው ምልክቶች ናቸው። ለምሳሌ፦ የእይታ ለውጥ፣ ብዝታ፣ የስሜት መታወክ፣ የመፍራት ስሜት
ታካሚዎች ራስ ምታቱን የሚያስነሳባቸውን ነገር ለይተው ቢያውቁ እና ቢጠነቀንቁ የራስ ምታቱ መደጋገም እንዲቀንስ ይረዳል። በተጨማሪ፡
- በቂ ውሃ መጠጣት
- እንደ ቡና ያሉ አነቃቂ ነገሮችን ያለማብዛት
- ጤናማ አመጋገብ
- በቂ እንቅልፍ መተኛት ህመሙን መቀነስ ላይ አስተቃጾ ያረጋሉ። ከዚህ በተጨማሪ፡ Paracetamol, ibuprofen የመሳሰሉትን የህመም ማስታገሻዎች መጠነኛ ራስ ምታት ሲኖር መጠቀም ይቻላል Sumatriptan የሚባለው መድሃኒት በጣም ጠንቀር ያለ ራስምታት ሲኖር ይሰጣል። ታካሚዎች በተደጋጋሚ በማይግሬን ሲጠቁ እና አኗኗራቸውን ሲጎዳ ረዘም ላለ ጊዜ ሚወሰዱ መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ። ይህ በአብዛኛው በሃኪሞ ሚወሰን ነው። እነዚህ መድሃኒቶች እስከ 8 ሳምንት ያህል ከተወሰዱ በኋላ ለውጥ የሚያመጡ ስለሆኑ በትእግስት መጠበቅ ይኖርቦታል።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።