ዳማከሴDamakese

ስብራት

  1. ምንድነው የአጥንት ተፈጥሯዊ ሁኔታን የሚያዛባ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በተለያዩ አካላዊ አደጋዎች ምክንያት ይፈጠራል። ሁሉንም ሰው በተለያየ የእድሜ ክልል ላይ ሊያጋጥም የሚችል ነው። ስብራት በተለይ ከ50 ዓመት እድሜ በኋላ የመከሰት እድሉ ከፍ ይላል። ሶስት አይነት ስብራት አለ(በመንስኤው ላይ በመነሳት)
  • በአካላዊ አደጋ ምክንያት የሚከሰት፡ ከፍተኛ ሃይል ያለው ምት በቀጥታ አጥንት ላይ ሲደርስ የሚፈጠር ስብራት ነው
  • በድግግም ምት የሚከሰት ፡ ይህ አነስ ያለ ሃይል በድግግም አጥንት ላይ ሲያርፍ የሚከሰት ሲሆን፤ በተለይ ደሞ አካላዊ ጥቃት በሚደርስባቸው ሰዎች ላይ በብዛት ይታያል።
  • ሌሎች የአጥንት ህመሞችን ተከትሎ የሚመጣ፡ ይህ የአጥንትን ተፈጥሯዊ ጥንካሬ የሚቀንሱ ህመሞችን ተከትሎ የሚፈጠር ስብራት ሲሆን፤ ኢንፌክሽን፣ የአጥንት ካንሰር፣የአጥንት መሳሳትን የመሳሰሉ ህመሞችን ተከሎ በተለይ ይታያል
  1. ምልክቶቹ
  • የተሰበረው አጥንት ላይ ከፍተኛ ህመም
  • የቦታው መቅላት እና ማበጥ
  • የተሰበረውን አካል ማንቀሳቀስ መቸገር
  • መበለዝ እና የተሰበረው አጥንት ቆዳን ቀዶ ሊታይ ይችላል
  1. ምርመራው
  • ተሰበረ ተብሎ የተጠረጠረውን አካል ኤክስሬይ(ራጅ) ማንሳት
  • የደም ምርመራ
  • አንዳንዴ እንደ ሃኪም ውሳኔ ሲቲ ስካን
  1. ህክምናው
  • በተለምዶ በሃገራችን እንደ ስብራት ያለ ጉዳት ሲከሰት ወደ ወጌሻ(የባህል ሃኪም) እየሄዱ ማሳሸት የተለመደ ነው። ይህ በጣም ጎጂ የሆነ ልምድ ነው። አጥንት ከተሰበረ ወደ ተፈጥሯዊ አቀማመጡ መመለስ እና እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ትክክለኛው የህክምና መንገድ ሲሆን በልምድ መታሸት አጥንቱን የባሰ ከተፈሯዊው ቦታ በማዛባት ጉዳቱን የበለጠ ይጨምራል። ስለዚህ እባኮን ስብራትን ከማሳሸት ይቆጠቡ!
  • በቀዶ ህክምና መጠገን
  • ብረት በማስገባት መደቦታው መመለስ
  • በሃኪም ተጎትቶ ወደ ቦታው ከተመለሰ በኋላ እንደ አሸዋ ያሉ ከበድ ያሉ ነገሮችን በመጠቀም ቦታውን እንዳይለቅ ማድረግ።

የህክምና አማራጩ እንደ ስብራቱ በሃኪም የሚወሰን ይሆናል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።