ስኬቢስ Sarcoptes scabiie በሚባሉ ጥቃቅን ምስጦች የሚፈጠር የሚያሳክክ የቆዳ ሽፍታ ነው። ምስጡ በሚፈነዳበት አካባቢ ኃይለኛ ማሳከክ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን ይህም በተለይ በምሽት ይብሳል። ታማሚውን እንቅልፍ የሚነሳ በሽታ ነው። ስኬቢስ በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ ነው እናም በቤተሰብ፣በትምህርት ቤት ክፍል፣ በአረጋውያን መንከባከቢያ ወይም እስር ቤት ውስጥ ከሰው ወደ ሰው ግንኙነት በፍጥነት ሊሰራጭ ይችላል። እከክ በቀላሉ ስለሚሰራጭ፣ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ብዙውን ጊዜ መላውን ቤተሰብ ወይም የቅርብ ወዳጆችን ለማከም ይመክራሉ።
- ከባድ ማሳከክ አብዛኛውን ጊዜ ምሽት ላይ የከፋ ነው።
- በቆዳው ላይ ከትንሽ ጉድፍቶች የተሠሩ ቀጫጭን ዋሻ መሳይ እብጠቶች
- በተለየ፤ የእግር እና የእጅ ጣቶች መካከል፣ብብት ውስጥ፣ሽንጥ ላይ የጡት ጫፍ ላይ እና ብሽሽት ላይ የበለጠ ይታያል።
- ንጽህናን መጠበቅ
- የተያዘ አንድ ሰው ካለ በቅርብ ያሉ ሰዎች እንዲታከሙ ማድረግ
- በሙቅ ውሃ ልብስን ማጠብ
- ማይታጠቡ ነገሮችን አሽጎ በማስቀመጥ ተባዩ ተርቦ እንዲሞት ማድረግ
- permerthin፡ ከአንገት በታች ሁሉንም የሰውነት አካል በደንብ በደንብ በመቀባት 8-14 ሰአት መቆየት
- benzyl bezoate ፡ ከ3-5 ተከታታይ ምሽቶች መቀባት
- Ivermectin ፡ ጠንከር ላለ ስኬቢስ የሚሰጥ መድሃኒት ነው።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።