ዳማከሴDamakese

የሽርት ውሃ ማነስ

ቃሉ እንደሚገልጸው የሽርት ውሃ መጠን ከተለመደው እና ለምቹ የጽንስ እድገት ከሚጠበቅው በታች ሲሆን የሚፈጠር ሲሆን በአልትራሳውንድ ምርመራ የሚለይ ህመም ነው። የሽርት ውሃ ጽንሱን በማህፀን ውስጥ የሚከብ ውሃ የሚመስል ፈሳሽ ነው። ጽንሱን ከኢንፌክሽን እና እምብርት መጨፍለቅ ይከላከላል እንዲሁም
በማህፀን ውስጥ እንደ ልቡ እንዲንቀሳቀስ ይረዳል። በተጨማሪም የሽርት ውሃ የጽንሱን የምግብ መፍጫ እና የመተንፈሻ አካላት ለማዳበር ይረዳል እንዲሁም የሙቀት መጠኑን ይቆጣጠራል። ይህ ህመም 4% የሚሆን እርግዝና ላይ የሚታይ ሲሆን በተልይም ደግሞ በመጨረሻ 3 የእርግዝና ወራት የበለጠ ይታያል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።